Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ለተሳተፉ አትሌቶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘዉዴ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ከተሳተፉ በኋላ በዛሬዉ ዕለት ማለዳ ወደ ኢትዮጵያ ለተመለሱ አትሌቶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ኢትዮጵያን በመወከል በየዉድድሩ ዘርፍ በተለይም በረጅም ርቀት ሩጫ ተሰልፈዉ የአቅማቸዉን በመፈጸም ወርቅን ጨምሮ ሜዳሊያ ላስገኙና በአጠቃላይ ለተወዳደሩት አትሌቶች በሙሉ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል፡፡

ፕሬዚዳንቷ የአትሌቶቹ የልምምድ ሥፍራ ላይ በመገኝትና በቤተ መንግሥት ሽኝት በማድረግ እንዳበረታቷቸዉ፣ መንግሥትም ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በመመደብ አትሌቶችን ለመደገፍና ለማብቃት ከፍተኛ ጥረት ማድረጉ አስታውሰዋል ፡፡

እንደ አሸኛኘቱ ሁሉ ሁኔታዉ እንዳመቸ ይፋዊ አቀባበል የሚዘጋጅ እንደሚሆንም ነው የገለጹት ፡፡

በቶኪዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያን ተሳትፎ በተመለከተ ፕሬዚደንቷ ዝርዝር ሪፖርት እንደሚጠበቁ ማስታወቃቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version