Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ቦርዱ ተተኪ ዕጩ ለማቅረብ የሚያስችል ውሣኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጷግሜ 01 ቀን 2013 ዓ.ም. ምርጫ ዕጩ ሆነው መቀጠል ለማይችሉ ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ተተኪ ዕጩ ለማቅረብ እንዲችሉ ውሣኔ አሳለፈ ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጷግሜ 01 ቀን 2013 ዓ.ም. ምርጫ ለሚያካሂድባቸው አካባቢዎች በተወዳዳሪ ፓርቲዎች በዕጩነት ቀርበው ነገር ግን ከዐቅም በላይ በሆነ ምክንያት ያቀረቧቸው ዕጩዎች ዕጩ ሆነው መቀጠል ለማይችሉ ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ተተኪ ዕጩ ለማቅረብ እንዲችሉ ቦርዱ የመጨረሻ ዕድል ለመስጠት ውሣኔ አስተላልፏል፡፡
በዚሁ መሠረት ከዛሬ ነሐሴ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት ሦስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ለቦርዱ የፖለቲካ የሥራ ክፍል ማመልከት የሚችሉ መሆናቸውን ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version