Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አሸባሪው ህወሓት ሰርጎ በመግባት ጥቃት እንዳይፈጽም እየተሰራ ነው – የሃይቅ ከተማ ከንቲባ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)አሸባሪው የህውሀት ቡድን ሰርጎ በመግባት የሽብር ጥቃት እንዳይፈጽም ለማድረግ የጸጥታ ሀይሉ ከህብረተሰቡ ጋር የተቀናጀ ስራ እየተሰራ መሆኑን በደቡብ ወሎ ዞን የሀይቅ ከተማ ከንቲባ አቶ ከበደ ካሳ ተናገሩ።

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከበደ ካሳ ሰርጎገቦችን ለመቆጣጠር 20 ኬላዎች ተቋቁመው ወጣቶችና የፀጥታ አካላት በቅንጅት አካባቢያቸውን እየጠበቁ ነው ብለዋል።

የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የለመደው አሸባሪው ጁንታ የህዝብን ሥነልቦና ለመረበሽ ሀይቅ ከተማን ጨምሮ ሌሎችን አካባቢዎች መቆጣጠሩን ገልጿል፤ ይህ ፍፁም ሀሰት ነው ሲሉም አክለዋል።

አስተዳደሩ ህብረተሰቡ የጁንታውን ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ ወደጎን ብሎ አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርቧል።

የፋና ጋዜጠኞች ቡድንም በከተማዋ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መኖሩንና ህዝቡ ከፀጥታ ሀይሎች ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ተመልክቷል።

የከተማዋ ወጣቶች በበኩላቸው÷ ጠላትን ለመደምሰስ እስከ ፍፃሜው በፅናት እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።

በከተማዋ 10 ሺህ የሚደርሱ ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ንፁሃን ዜጎች የሚገኙ ሲሆን÷ የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ ጥረት እያደረገ መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version