አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የገጠማትን የህልውና አደጋ ለመመከት ዝግጁ መሆኑን የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አስታወቀ።
መኢአድ አሸባሪው የህወሓት ቡድን እያደረሰ ያለውን አገር የማተራመስና የሽብር ተግባር አስመልክቶ ለኢዜአ በላከው መግለጫ፥ አሸባሪው ህወሓት እየፈጸመ ካለው አገር የማተራመስና የሽብር ተግባር ለመታደግ አባሎቹንና ደጋፊዎቹ ከመከላከያ ጎን ለመሰለፍ ዝግጁ ናቸው።
የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ደም በመለገስ ለሰራዊቱ ያላቸውን አጋርነት አሳይተዋል፤ ድጋፋቸውንም አጠናክረው ይቀጥላሉ ብሏል የፓርቲው መግለጫ።
ፓርቲው አሸባሪው ህወሓት ለ30 ዓመታት ሲያካሂደው የነበረውን የከፋፈለህ ግዛ ስርዓት በሰላማዊ መንገድ ሲታገል መቆየቱንም አስታውሷል።
መኢአድ የአገርን ህልውና ለማስቀጠል የፖለቲካ አጀንዳዎቹን በይደር ይዞ የአገር አድን ትግሉን በይፋ መቀላቀሉን አስታውቋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

