Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የዓለም ጤና ድርጅት ሦሥት በሙከራ ላይ የሚገኙ የኮቪድ 19 መድኃኒቶችን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት÷ በኮቪድ 19 ቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸውን ሊያጡ የሚችሉ ሰዎች ቁጥር ይቀንሳል ያላቸውን ሦሥት በሙከራ ላይ ያሉ መድኃኒቶች ይፋ አደረገ፡፡

በሙከራ ላይ ያሉት መድኃኒቶችም አርቴሱኔት፣ ኢሜቲኒብ እና ኢንፊሊክሲማብ እንደሆኑ ነው የተገለፀው፡፡ መድኃኒቶቹ በቀጣይ በ 52 ሀገራት የኮቪድ 19 ታማሚዎች ላይ ተሞክረው ውጤታማ ከሆኑ ጥቅም ላይ እንደሚውሉም ነው የተገለፀው፡፡

መድኃኒቶቹ አዲስ እንዳልሆኑና ሌሎች በሽታዎችን ለማከም ጥቅም ላይ እየዋሉ እንደሚገኝም ነው የተመለከተው፡፡

በዓለም ላይ እስካሁን በኮቪድ 19 ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ204 ነጥብ 28 ሚሊየን ሲልቅ በቫይረሱ ሕይወታቸውን ያጡ ደግሞ ከ 4 ነጥብ 31 ሚሊየን በላይ እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ምንጭ÷ሲጂቲ ኤን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Exit mobile version