አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዋሽና ዋቢ ሸበሌ ተፋሰስ የዩኒቨርሲቲዎች ፎረምና በታላቁ የህዳሴ ግድብ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሀገራዊ አውደ ጥናት በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀምሯል ።
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት የሚካሄደው አውደጥናት ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን÷ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚዳንት ዶክተር ጀማል ዩሱፍ በሁለቱ ተፋሰሶች ወስጥ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት በምርምር በተደገፈ መልኩ መደገፍ ዓላማው ያደረገ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙት ዳይሬክተር አቶ አለምሸት ተሾመ በበኩላቸው÷ በዚህ ጉባዔ የአዋሽና ዋቢሸበሌ ወንዞችን ለሀገር ጥቅም ለማዋል በወንዞቹ ተፋሰስ ውስጥ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተባብረው ለመስራት ፎረም የሚመሰረትበት እንደሆነ አስታውቀዋል ።
በነስሪ ዩሱፍ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

