አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በአማራ ክልል በደብረ ታቦርና በኦሮሚያ ክልል በበቆጂ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል የማከፋፈያ ጣቢያዎች ግንባታ እንደሚያከናውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገለፀ።
በ20 ነጥብ 9 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪም የኃይል የማከፋፈያ ጣቢያዎቹ ግንባታ እንደሚከናወን ታውቋል፡፡
የደብረ ታቦር ባለ 230/33/15 ኪሎቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ከባህር ዳር – አላማጣ ከሚሄደው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር የሚጠለፍ ሲሆን÷ የበቆጂ ማከፋፈያ ጣቢያ ከመልካ ዋከና – ቆቃ ከተዘረጋዉ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተጠልፎ የሚገነባ ነው ተብሏል፡፡
ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ በከተሞቹና በአቅራቢያቸው ለሚገኙ ከተሞችና ወረዳዎች አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ እንደሚያግዝ ኢፕድ ዘግቧል፡፡
የግንባታ ስራው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኮንስትራክሽን ያከናውነዋል ተብሏል፡፡
በተያያዘም የጉራራ፣ ጎፋና መካኒሳ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ግንባታ እንዲሁም ሁለት የባለ 132 ኪሎቮልት ማስተላለፊያ መስመሮችን አቅም የማሳደግ ስራ ለማከናወን እንቅስቃሴ መጀመሩን ተቋሙ አስታውቋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

