Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመኖሪያ ቤት የተከማቸ በርካታ ቦንዳ ልባሽ ጨርቅ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 07፣ 2013 ኤፍ ቢ ሲ) በህገ ወጥ መንገድ በመኖሪያ ቤት የተከማቸ በርካታ ቦንዳ ልባሽ ጨርቅ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ልባሽ ጨርቁ የኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ እና የኢንተርፖል ኦፕሬሽንና ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ዲቪዥን ከህብረሰቱ በደረሰ ጥቆማ ባደረጉት ክትትል ነው በቁጥጥር ስር የዋለው፡፡
383 ጥቅል ቦንዳ ህገ ወጥ ልባሽ ጨረቁ በኮልፌ ቀራኒዮ ሎሚ ሜዳ አካባቢ ወረዳ 13 እና 14 እንዲሁም ውንጌት በረኪና ፋብሪካ ገባ ብሎ በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ውስጥ እንደገባና በሶስት መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ተከማችቶ መገኘቱን ኢንተርፖል ኦፕሬሽንና ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ዲቪዥን ሃላፊዋ ኢ/ር ጥሩወርቅ መንግስቴ ገልጸዋል፡፡
የቦንዳ ልብሱ ሊያዝ የቻለው የማህበረሰብ ጥቆማን መሰረት በማድረግ ከጉሙሩክ፣ ከመድሃኒትና ቁጥጥር ባለስልጠናትጋር በጋራ ዳሰሳዊ ጥናት በማካሄድ መሆኑን ኢንስፔክተሯ ተናግረዋል፡፡
በቁጥጥር ስር የዋለው ቦንዳ ልብሰም ከ3 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው መሆኑን ከፌዴራልፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉና የገበያ ሁኔታው እንዳይረጋጋ የሚያደርጉ ነገሮችን ህብረተሰቡ ሲመለከት ለህግ አስከባሪ አካላት ፈጥኖ ጥቆማ መስጠት እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version