Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሚኒስቴሩ 360 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዷል

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የገቢዎች ሚኒስቴር በ2014 በጀት ዓመት 360 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለፀ፡፡
ስትራቴጂክ ፕላንና ፕሮጀክት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ታደሠ ዕቅዱን ለተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች አቅርበዋል፡፡
እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ በጥቅል ከታቀደው 360 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ከታቀደው ውስጥ የገቢው ምንጭ ከሀገር ውስጥ ታክስ 205 ቢሊየን ብር፣ ከጉምሩክ ቀረጥና ታክስ 154 ነጥብ 8 ቢሊየን ብርና ቀሪው ከሎተሪ ሽያጭ የሚሰበሰብ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አንዱ የዕቅዱ መነሻ መሆኑና ገቢን በብቃት ለመሰብሰብ በቴክኖሎጂ የተደገ አሰራር ትኩረት ተሰጥቷቸው ተግባራዊ እንደሚደረጉ ዳይሬክተሩ መናገራቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version