አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪው ህወሃትን ሰርጎ ገቦች ለመከላከል በተቀናጀ መልኩ እየተሰራ መሆኑን በደቡብ ወሎ ዞን የአምባሰል ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ምክትል ኮማንደር መኮንን ሹሙ ተናገሩ።
የጠላትን አሰላለፍና ሰርጎ መግባት ለመከላከል በመከላከያ ሰራዊት በልዩ ሀይሎች፣ሚሊሻዎች፣ የአካባቢው ነዋሪዎች በተቀናጀ መልኩ እየተሰራ ይገኛል።
ህብረተሰቡ ሰርጎ ገቦችን እንዲከላከል ወጥ የመረጃ ፍሰት ስርዓትም ተዘርግቷል ተብሏል።
በአምባሰል ወረዳ ውጫሌ ከተማም ከ700 በላይ ወጣቶች መሰረታዊ ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ወደ ስራ መግባታቸው ተገልጿል፡፡
አሸባሪው የህወሃት ቡድን ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል በሚል መርህ ተደጋጋሚ የሀሰት መረጃዎችን እንደሚለቅ የተገለፀ ሲሆን÷ ሀሰተኛ መረጃዎቹ ከእውነታው ጋር የተጣረሱ ናቸው ብለዋል።
በአፈወርቅ እያዩ እና በለይኩን አለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

