Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሶማሌ ክልል የትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ከሶማሊያ የትምህርት ዘርፍ አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሶማሊያ የተለያዩ ግዛቶች የተውጣጡ የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ አመራሮች በጅግጅጋ ከተማ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
 
የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ መሀመድ ፋታህ ÷ አመራሮቹ በሶማሌ ክልል ያደረጉት ጉብኝት በትምህርቱ ዘርፍ ያለውን መልካም ተሞክሮ ለመቅሰም ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
ለአመራሮቹ የክልሉ የትምህርት ቢሮ አለማና ራዕይ ፣ የቢሮው ተቋማዊ አደረጃጀት፣ በሀገሪቱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ እና በክልሉ እየተካሄደ የሚገኘው አጠቃላይ የትምህርት ስራዎች ዙሪያ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
 
አቶ መሀመድ ፋታህ ÷በአሁኑ ጊዜ በክልሉ በርካታ ኮሌጆችንና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚገኙ ጠቁመው ቢሮው በትምህርቱ መስክ
ጎረቤት ሶማሊያን ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል ።
 
የሶማሊያ የቴክኒክ ትምህርት ስልጠና እና ኢ-መደበኛ ትምህርት ዳይሬክተር አቶ አብዲአዚዝ ኑር ÷ በክልሉ አጠቃላይ የትምህርት ስራዎች በተለይም በቴክኒክና ሞያ፣ በሴቶች ትምህርት፣ በጎልማሶች ትምህርትና አመራጭ መሠረታዊ ትምህርት አሰጣጥ ላይ ያለውን መልካም ተሞክሮ ለመቅሰም መምጣታቸውን ገልጸዋል።
 
በክልሉ ባደረጉት ጉብኝት ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ከፍተኛ ሀላፊዎች ጋር ስኬታማ ውይይት ማድረጋቸውን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ በክልሉ ያሉ ኮሌጆች የትምህርትና ስልጠና ስራዎችን በመጎብኘት ጥሩ ልምድ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
 
ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ከፍተኛ ሀላፊዎች ጋር ስኬታማ ውይይት ማድረጋቸውን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ በክልሉ ያሉ ኮሌጆች የትምህርትና ስልጠና ስራዎችን በመጎብኘት ጥሩ ልምድ እንዳገኙ መናገራቸው ከሶማሌ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
የክልሉ የትምህርት ዘርፍ የተለያዩ የስራ ሀላፊዎች በበኩላቸው÷ የሶማሊያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ የትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ ያደረጉት ጉብኝት በቀጣይ በትምህርቱ መስክ ተባብሮ ለመስራት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
Exit mobile version