አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ፣ የጋምቤላ እና የቤንሻንጉል ጉመዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች በጋራ የልማት እና የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡
በዉይይቱ ሶስቱ ክልሎች በምዕራብ ኢትዮጵያ የህዝቦችን ወድማማቸነት ለማጠናከር፣ የጋራ ልማት እና ጸጥታን ለማረጋገጥ አቅደዉ እየሰሩ መሆኑና እስካሁን ባለዉ ሂደትም አበረታች ለዉጦች መመዝገብ መጀመራቸዉ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም የህዝቦችን ጥቅም ሊያረጋግጡ የሚችሉ በርካታ የልማት ስራዎች መሰራታቸዉ እና የፀጥታ ሁኔታ ላይም አንጻራዊ መሻሻሎች እየመጣ እንዳለ ተገምግሟል፡፡
በዚህ ረገድ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረዉ እንዲቀጥሉ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
በሌላ በኩል አመራሮቹ በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታና የምዕራብ ኢትዮጵያን ፀጥታ በተመለከተ በመወያየት ከፌዴራል የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በጁንታዉ ተላላኪዎችና የጠላት ሰርጎ ገቦች ላይ የተቀናጀ እርምጃ በመዉሰድ የአከባቢዉን ሰላም ለማረጋገጥ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡
በዉይይት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፋንታ ና ሌሎች የክልሎች እና የፌዴራል መንግስት የፀጥታ አካላት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

