አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአምቦ ከተማ 1 ሺህ 377 ተተኳሽ ጥይቶች በህገ ወጥ መንገድ በተሽከርካሪ ጭነው ሲያጓጉዙ የተገኙ አራት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።
ግለሰቦቹ ጥይቶቹን የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 4-28212 ኢት በሆነ አምቡላንስ ተሽከርካሪ ጭነው ሲያጓጉዙ እንደተገኙ የከተማዋ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሲሳይ ሂርጳ ገልጸዋል።
ከከተማዋ ወጣ ብሎ በሚገኘው አዋሮ ቆራ አካባቢ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ትናንት ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ30 አካባቢ ነው ግለሰቦችን ከነጥይቶቹ መቆጣጠር የተቻለው ብለዋል።
ኮማንደር ሲሳይ እንዳመለከቱት ግለሰቦቹ ጥይቶቹን በአልባሳት ጠቅልለው በማዳበሪያ ውስጥ መድሃኒት አስመስለው በመጫን ከቡራዩ ከተማ ወደ አምቦ ለማሳለፍ ሲሞክሩ ነው የተደረሰባቸው።
በዚህም አሽከርካሪው፣ ፋርማሲስት እና ሁለት የጥይቱ ተቀባዮች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳዩ እየተጣራ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ፖሊስ ህገወጥ እንቅስቃሴን ለመከላከል በሚያደርገው ጥረት ኅብረተሰቡ አጥፊዎችን በመጠቆም የድርሻውን እንዲወጣም ኮማንደር ሲሳይ ጠይቀዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

