አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የታንዛንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊቤራታ ሙላሙላን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
በውይይታቸው ሀገራቱ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ማጠናከር በሚችሉባቸው እና በሴቶች ተሳትፎ ዙሪያ መወያየታቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤትያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከ6 ወራት በፊት በታንዛንያ የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸውና የወቅቱ ፕሬዚዳንት ማጉፉሊ በድንገት ከማረፋቸው በፊት ያገኟቸው የመጨረሻ ርዕሰ ብሔር መሆናቸው ይታወሳል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

