Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አልጄሪያ ከሠደድ እሳት አደጋዎች ጋር በተያያዘ 22 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አዋለች

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አልጄሪያ በደኖቿ ላይ ከተከሰቱት የሰደድ እሳት አደጋዎች ጋር በተያያዘ የጠረጠረቻቸውን 22 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሏ ተገለፀ፡፡

ሀገሪቱ በቁጥጥር ስር ያዋለቻቸው ግለሰቦች ተቀጣጣይ ቁሶችን ተጠቅመው አደጋውን አድርሰዋል ብላ የጠረጠረቻቸውን መሆኑ ታውቋል፡፡

ከሰኞ ጀምሮ በሰሜን አልጄሪያ ከ12 በላይ የሠደድ እሳት አደጋዎች እንደተከሰቱ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ከዋና ከተማው አልጀርስ በስተምሥራቅ የሚገኘውን የካቢሊ ጥቅጥቅ ደን፣ አደጋዎቹ በተደጋጋሚ የደረሱበት እንደሆነም ነው የታወቀው፡፡

በወቅቱም የአካባቢው ባለሥልጣናት ከቃጠሎው ጀርባ ተቀጣጣይ ቁሶችን የተጠቀሙ ግለሰቦች እጅ ሳይኖርበት እንዳልቀረ የነበራቸውን ጥርጣሬ ገልፀው ነበር፡፡

እስካለፈው ረቡዕ ድረስም በሰደድ እሳት አደጋው የ42 ሰዎች ሕይወት ማለፉ መገለፁ የሚታወስ ሲሆን ÷አሁን ላይ ቁጥሩ 69 መድረሱ ተረጋግጧል፡፡

ምንጭ ፡-አልጀዚራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version