Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኮሚሽኖቹ በደሴ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የሰብዓዊ ድጋፍ ማቅረብ ጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራርና የአማራ ክልል ምግብ ዋስትና ኮሚሽኖች በደሴ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የሰብዓዊ ድጋፍ ማቅረብ ጀምረዋል ።
በተጨማሪም በደሴ ከተማ የሚገኙ የግል ጤና ዘርፍ ተቋማት ከ621 ሺህ ብር የሚያወጡ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርገዋል።
የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር የአደጋ ምላሽና ክትትል ሃላፊው አቶ ታዬ ጌታቸው፥ 31ሺህ 4 ሰዎች ተመዝግበው ድጋፍ ያገኛሉ ብለዋል።
የተፈናቃዮች ቁጥር በየእለቱ እየጨመመረ መምጣቱንም ተናግረዋል፡፡
መንግስት የዜጎችን እንግልት ለመቀነስ ይሰራል ያሉ ሲሆን፥ ሁሉም የየድርሻውን ማበርከት እንዳለበትም አሳስበዋል።
የወሎ ግንባር ሞብላይዜሽንና ህዝብ ግንኙነትት ሀላፊ አቶ ወንዳለ ሀብታሙ፥ በህዝብ ላይ ጦርነት የከፈተው አሸባሪው ቡድን ለብዙዎች እንግልት ምክንያት ሆኗል ነው ያሉት።
ግንባር ከሚደረገው ዘመቻ በተጨማሪ በመደጋገፍ ይህን ጊዜ ማለፍ ይገባልም ነው ያሉት ።
አቶ ወንዳለ አክለውም ቡድኑ ሰርጎ በመግባት ዝርፊያ፣ ግድያና ሌሎች አስነዋሪ ድርጊቶችን መፈፀሙን አስረድተዋል።
ህዝብን ለማዋረድ የሚደረገውን ጥረት ለማክሸፍም ወጣቶች አሁንም ወደ ስልጠናና ወደ ግንባር መሄድ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የወሎ ህዝብና ሁሉም ኢትዮጵያንም እያሳዩ ያሉት መደጋገፍ የሚመሰገን ነው ያሉ ሲሆን፥ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
አሸባሪ ቡድኑ በግፍ ያፈናቀላቸው ወጣቶች ዘመቻውን እንደተቀላቀሉም ገልፀዋል።
አሸባሪ ቡድኑ የሁሉም የኢትዮጵያዊያን ጠላት በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን አንድነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸውን ተጠቁሟል።
በአፈወርቅ እያዩና ለይኩን ዓለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
37
Engagements
Boost Post
34
1 Comment
2 Shares
Like
Comment
Share
Exit mobile version