አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን የዘማች አርሶአደሮች ሰብል እየታረመ መሆኑ ተገለፀ፡፡
ዞኑ ደሴ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮች የሀገርን ክብርና ህልውና ለማስጠበቅ ግንባር ድረስ የተጓዙ ቤተሰቦችን ሰብል እየተንከባከቡ ይገኛሉ።
ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስተያየታቸውን የሰጡ አርሶ አደሮች ሀገር የገጠማትን ፈተና ለመሻገር መተባበር ያስፈልጋል ይህንንም እየተገበርን ነው ብለዋል።
አሸባሪው ጁንታ የግብርና ዋነኛ ወቅትን ጠብቆ ጦርነት መክፈቱ ህዝብ ላይ ጫና ለማሳደር ማለሙን ያሳያል ያሉት አርሶ አደሮቹ ይህንን ለመመከትም በጋራ እንቆማለን ነው ያሉት።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታና የወሎ ግንባር የህዝብ ግንኙነትና የሞብላይዜሽን ሀላፊ አቶ ወንዳለ ሀብታሙ አሸባሪው ቡድን ሁሉን አቀፍ ጥቃት መክፈቱን ተናግረዋል።
ወቅቱ የግብርና ስራ የሚከወንበት መሆኑን ገልፀው በዚህ ወቅት ከራስ በፊት ሀገርን አስቀድመው ወደ ግንባር የዘመቱ ቤተሰቦችን ምርት የመንከባከብ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
አሸባሪውን ቡድን ከመመከት ባለፈ መደበኛ የልማት ስራዎች እንዳይስተጓጎሉ መንግስት እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።
በአፈወርቅ እያዩና በለይኩን ዓለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

