አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪውን ህወሓት ለመደምሰስ በጦር ሜዳ ገድል እየሰሩ ለሚገኙ ጀግኖች ስንቅ በወሎ ዩኒቨርሲቲ እየተዘጋጀ ነው።
የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች ሕይወት ለሚሰጡን ጀግኖች ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በማድረግ የአሸባሪውን ቡድን ፍፃሜ እናፋጥናለን ብለዋል።
በዚህም ደረቅ ምግቦችን በማዘጋጀት፣ የዘማች ቤተሰቦችንና ተፈናቃዮችን በመደገፍና በማበረታት ላይ እንደሚገኙም ነው ያስረዱት፡፡
የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶክተር አፀደ ተፈራ ሁሉም የሚኖረው ሀገር ስትኖር በመሆኑ የድጋፍ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልፀዋል፡፡
በአፈወርቅ እያዩና በለይኩን ዓለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

