አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጁንታው ሃይል በአፋር በኩል እየተሽመደመደ ይገኛል።
በአፋር በኩል አራት ወረዳዎች ወረራ ለመፈጸም በሞከረው የሽብር ቡድን ላይ የጸጥታው ሃይል የማያዳግም እርምጃ እየወሰደበት እንደሚገኝ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት የገለጹት የአፋር ልዩ ሃይል አዛዥ ረዳት ኮምሽነር መሃመድ ሲራጅ ፥በክልሉ ህዝብ ከጸጥታው ሃይል ጎን ተሰልፎ ጁንታውን አደብ እያስገዛው ነውም ብለዋል ።
በርካታ የጁንታው ሃይል መማረካቸውን ያነሱት ዋና አዛዡ ፥ጁንታው ከባድ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ጥሎ መፈርጠጡንም ተናግረዋል።
በአወል አበራ እና ጥበበስላሴ ጀምበሩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

