Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በልዩ ዘመቻዎች ሃይል ማሰልጠኛ ማዕከል የመሰረታዊ ውትድርና የስልጠና መክፈቻ ስነ-ስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በልዩ ዘመቻዎች ሃይል ማሰልጠኛ ማዕከል የመሰረታዊ ወትድርና የስልጠና መክፈቻ ስነ-ስርዓት ተካሄደ፡፡

የማሰልጠኛ ማዕከሉ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ዋለልኝ ታደሰ÷ በትልቅ ሞራልና ወኔ እምቢ ለሀገሬ ብለው ሀገራቸውን በቅንነትና በታማኝነት ለማገልገል ክቡር የሆነውን የውትድርና ሙያ ለመቀላቀል ከተለያዩ የሀገራችን ጫፍ በመክተታቸው ምስጋና አቅርበዋል።

ሽብርተኛውን የጁንታ ቡድን ለመደምሰስ በማሰልጠኛ ማዕከሉ የሚሰጡትን ወታደራዊ ስልጠናዎችንና ወታደራዊ ሳይንሶችን ከእውቀት ጋር በመደመር ስልጠናችሁን በተገቢው ሁኔታ በማጠናቀቅ ሀገር ከእናንተ የምትፈልገውን ሁሉ አሟልታችሁ ማገልገል ይጠበቅባችኋል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version