አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ፍጹም አሰፋ በቅርቡ በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት ፈቃድ ካገኘው የዓለም አቀፍ ጥምረት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ዶክተር ፍጹም ኢትዮጵያ በቀጣይ በግሉ ዘርፍ ላይ ስላቀደችው የማሻሻያ እርምጃም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የፕላን እና ልማት ኮሚሽን ባዘጋጀው የአስር ዓመት እቅድ ላይ በኢንቨስትመንት፣ የስራ ዕድል ፈጠራ፣ ቴክኖሎጂ እንዲሁም በሌሎችም ዘርፎች ላይ ለማሳካት የታለሙ ውጥኖችንም ያነሱ ሲሆን እቅዱ ከግል ዘርፍ አንፃር ያስቀመጠውን እና መንግስት በግል ዘርፉ ላይ ያለው የልማት ዕድልና አቅጣጫን በተመለከተም አንስተዋል፡፡
በተጨማሪም የዓለም አቀፍ ጥምረት ለኢትዮጵያ ተወካዮች ማብራሪያ በጠየቁባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጎ ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡
የጥምረቱ ተወካዮች ከኮሚሽነሯ ጋር የነበራቸው ውይይት የመንግስትን አቅጣጫ ለመረዳት እና ኢትዮጵያ ከዘርፉ የምትጠብቀውን ለማወቅ መልካም እድል የፈጠረላቸው መሆኑን መግለፃቸውን ከፕላን እና ልማት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

