Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የግብርና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የግብርና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች እና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ35 ሚሊየን ብር በላይ ለገሱ፡፡
በተጨማሪም ለመከላከያ ሰራዊቱ ደም የለገሱ ሲሆን÷ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ከ35 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ዓይናለም ንጉሴ ÷የሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች እና ሰራተኞች በቀጣይም የሚጠበቅባቸውን ማንኛውንም ድጋፍ በማድረግ አገራዊ ግዴታቸውን እንደሚወጡ መናገራቸውን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version