Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በቀጣይ ሶስት ዓመታት ተወዳዳሪ እና የተሻለ አገልግሎት ለደንበኞቼ አቀርባለሁ- ኢትዮ ቴሌኮም

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣይ ሶስት ዓመታት ተወዳዳሪ እና የተሻለ አገልግሎት ለደንበኞቹ ለማቅረብ ዝግጅት ማድረጉን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 ዓ.ም ቢዝነስ እቅዱ÷ ለደንበኞቹ ለማቅረብ ባቀዳቸው አዳዲስ እና የተሻሻሉ ምርት እና አገልግሎቶች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ለቀጣይ ዓመታት ስለ ተቋሙ እቅድ ለሚዲያወች ገለፃ ያደረጉ ሲሆን÷ ”ድልድይ” የተሰኘ የሶስት ዓመት እቅድ በማውጣት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

እቅዱ የሰራተኞችን እና የደንበኞችን እርካታ መሰረት በማድረግ የተሻለ አገልግሎት በመስጠት ተቋሙን ትርፋማ ለማድረግ ያስችላልም ነው ያሉት፡፡

ወቅቱን ታሳቢ በማድረግ ተለዋዋጭ እቅዶች ታቅዷል ያሉት ስራ አስፈጻሚዋ፥ እቅዱ የተለያዩ ጉዳዮችን ታሳቢ ያደረገ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡

በሚቀጥለው አመት ወደ ገበያው ይቀላቀላል የተባለው በከፊል የግል ኦፕሬተር ጋር ተወዳዳሪ መሆን፣ የመሰረተ ልማት ማጋራት እና የሰሜኑን ኢትዮጵያ ወቅታዊ ችግር ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም የልማት ድርጅት እንደመሆኑ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅቷልም ብለዋል ስራ አስፈጻሚዋ፡፡

አገልግሎቱን ዲጅታል በማድረግ ደንበኞችን በቀላሉ አገልግሎት እንዲያገኙ እየተሰራ ስለመሆኑም ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version