Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ለትግራይ ክልል ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገች

ABU DHABI, 18th August, 2021 (WAM) -- The UAE, in cooperation with the World Food Programme (WFP), has sent an aircraft carrying food supplies to the city of Mek'ele in Tigray region, Ethiopia, to support the humanitarian effort and help to address quickly the needs of thousands of civilians. Wam

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ለትግራይ ክልል ተፈናቃዮች የምግብ ድጋፍ ማድረጓ ተገለፀ፡፡
ሃገሪቱ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ነው 200 ቶን አስፈላጊ የሆኑ የምግብ አቅርቦቶችን የጫኑ አውሮፕላኖችን ልካለች።
እርዳታውም በክልሉ በነበረው ህግ የማስከበር ዘመቻ እና ከኮቪድ19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ለተጎዱ ዜጎች የሚውል መሆኑን ዘ ናሽናል ኒውስ ዘግቧል፡፡
በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች አምባሳደር መሃመድ አል ራሺዲ የተባቡሩት አረብ ኢሚሬቶች በትግራይ ያለውን የሰብዓዊ ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት በክልሉ የምግብ አቅርቦት ዝቅተኛ ሲሆን፥ የዓለም የምግብ መርሃ ግብርም ከተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የአትክልት ዘይት ከሌሎች የምግብ፣ የነዳጅ እና የሰብዓዊ አቅርቦቶች ጋር በተቻለ ፍጥነት ለማድረስ ማቀዱም ተነግሯል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version