Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የቻይና መከላከያ ሚኒስቴር የኮቪድ 19 ክትባት መድሀኒት ለሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና የመከላከያ ሚኒስቴር 200 ህሺ ዶዝ ሲኖቫክ የኮቪድ19 ክትባት መድሀኒት ለኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉ ለ150 ሺህ ሰዎች ሙሉ ክትባት መስጠት እንደሚያስችል የመከላከያ ጤና ማበልጸግ እና የበሽታ መከላከል መምሪያ ሀላፊ ተወካይ ኮሎኔል ዶክተር አለሙ ትኬ በርክክቡ ወቅት ተናግረዋል።
በግንባር ላይ ተሰማርቶ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ክትባቱን ለማጓጓዝና ለማዳረስ ከኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
ለተደረገው ድጋፍም ምስጋና ማቅረባቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የቻይና የመከላከያ ሚኒስቴር ባለፈው ግንቦት ወር 100 ሺህ ዶዝ የኮቪድ 19 ክትባት ድጋፍ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version