አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ)በሽብርተኛው ህውሃት ለተፈናቀሉ ከ376 ሺህ በላይ ወገኖች የሰብአዊ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
ከፋና ብሮድካስቲነግ ኮርፖሬታ ጋር ቆይታ ያደረጉት የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ÷ በተለይም ሽብርተኛው ህወሃት በአማራ እና አፋር ክልሎች ባደረሰው ጥቃት ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን ገልጸዋል።
በአማራ ክልል 300ሺህ እና በአፋር ክልል 76 ሺህ ለተፈናቀሉ ዜጎችም የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች መቀጠላቸውን አንስተዋል።
አለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች ግን በሚፈለገው ልክ ለተፈናቃዮቹ ድጋፍ ማድረግ ላይ ውሰንነት ይታይባቸዋልም ነው ያሉት ኮሚሽነሩ።
በቀጣይም ከረጂ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት ለመስራት ትኩረት ስለመሰጠቱ አንስተው÷ በአሁኑ ወቅት መንግስት ሙሉ ድጋፉን ብቻውን እያደረገ ነው ብለዋል ።
በአጠቃላይም በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር 11ሚሊየን ደርሷል።
በሀይለየሱስ መኮንን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

