Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አሸባሪው ህወሓት “ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ” እንቅስቃሴ የአገር ክህደት መሆኑን የጌታቸው ረዳ ወንድም ሃይለ ረዳ ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 14 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)አሸባሪው ህወሓት “ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ” በማለት እንቅስቃሴ መጀመሩ የአገር ክህደት መሆኑን የአሸባሪው ህወሓት  ቃል አቀባይ የጌታቸው ረዳ ወንድም ሃይለ ረዳ  ገልጸዋል፡፡

በአፋር ክልል ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ዜጋ መምህሩ ሃይለ ረዳ፤ አሸባሪው ህወሃት የትግራን ህዝብ ከአጎራባች ክልሎች ጋር ደም ለማቃባት ትንኮሳ ማድረጉ ፍፁም ተቀባይነት የለውም ሲሉም  ገልጸዋል።

የሽብር ቡድኑ የአገር ዳር ድንበር የሚጠብቀውን የአገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝን ድንገት በማጥቃት የፈፀመው ዘግናኝ ድርጊትም በየትኛውም መልኩ ተቀባይነት እንደሌለው ተናግረዋል።

“በኢትዮጵያ አላስፈላጊ ግጭትና ጦርነት እንዲካሄድ አሸባሪው ህወሓት ቆርጦ በመነሳት የችግሮች ሁሉ ምክንያት ሆኗል” ብለዋል።

ከዚህም ባለፈ የትግራይን ህጻናት ለጦርነት መልምሎ በማሰለፉ ከፍተኛ ወንጀል እየፈፀመ ይገኛል ነው ያሉት መምህር ሃይለ ረዳ።

የግለሰቦችን ስልጣን ለማስጠበቅ ሲባል ህፃናትን ለጦርነት በማሰለፍ ህይወታቸው እንዲቀጠፍ በማድርግ የትግራይ ክልል ነዋሪ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዲገባ እያደረጉት መሆኑን አመልክቷል።

በአፋር ጋሊኮማ ንጹሃን ዜጎችን በመጨፍጨፍ የሽብር ቡድኑ የፈፀመውን የጭካኔ ተግባርም ማውገዛቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version