አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኮኖሚ አሻጥር በመፍጠር ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
ሰው ሰራሽ የምርት አቅርቦት እጥረት በሚፈጥሩና የህዝቡን የተረጋጋ ኑሮ ለማወክ ብሎም ሃገር ለማፍረስ በሚሰሩና እንዲሁም በሚተባበሩ የህዝብና የሃገር ጠላቶች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡
ዛሬ ይህንን ተግባር በበላይነት የሚመራና የሚከታተል በፌዴራል መንግስት እና በከተማ አስተዳደሩ የተዋቀረ ግብረሃይል መቋቋሙም ነው የተገለፀው፡፡
በመሆኑም መላው የመዲናዋ ነዋሪ በዚህ ህገወጥ ተግባር ላይ እየተሳተፉ ያሉ ተቋማትና ግለሰቦችን በመጠቆምና በማጋለጥ እንደከዚህ ቀደሙ አብሮ እንዲሰራ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ጥሪ አቅርበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

