Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሻሸመኔ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሻሸመኔ ከተማ ትላንትና ማታ ከሌሊቱ 5 ሰዓት አካባቢ  በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት አልፏል።

የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ዘርፍ ቁጥጥር ሀላፊ ኮማንደር ኡመር ከራሞ ለጣቢያችን እንደተናገሩት፥  አደጋው የደረሰው ሁለት የጭነት መኪናዎች እንጨት ጭነዉ ከሁለት አቅጣጫ ወደ አደባባይ ሲጓዙ  በመጋጨታቸዉ  ነው።

አይሱዙ የጭነት መኪና ከኮፈሌ አቅጣጫ ወደ መሀል ከተማ ሲነቀሳቀስ፣ ሌላኛዉ ኤሮትራከር ከሀዋሳ ከተማ አቅጣጫ  እንጨት በመጫን ወደ አዲስ አበባ መስመር ሲንቀሳቀስ የነበረ ጋር በመጋጨት ነዉ አደጋዉ የደረሰዉ።

በአደጋዉ መኪኖቹ ዉስጥ የነበሩት 5 ሰዎች የሞቱ ሲሆን፥ ሁለቱ መኪኖች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ከኮማንደር ኡመር ያገኘነዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ ከኮፈሌ በኩል የመጣዉ አይሱዙ የጭነት መኪና የለሊት ጸጥታ ተቆጣጣሪ ፖሊስ ሲያስቆሙት ጥሶ አልፏል።

በዚህም አደባባይ ላይ ሲደርስ የራሱን መስመር ሙሉ በሙሉ በመልቀቅ ከሲኖትራኩ ጋር በመጋጨት አደጋዉን አሰቃቂ እንዲሆን አድርጎታል።

በምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ህገወጥት የእንጨት ዝዉዉር ያለ ሲሆን፥ በ2013 በጀት አመት ብቻ በዚህ ሁኔታ የተደረሰባቸዉና የህግ ቅጣት የተወሰነባቸዉ 132 እንደሆኑ ከዞኑ የአከባቢ ጥበቃ፣ ደንና አየር ንብረት ለዉጥ ባለስልጣን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

በጌታቸዉ ሙለታ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version