አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት 3 ሚሊየን ብር ገንዘብ በማሰባሰብ ድጋፍ አደረገ ።
ዩኒቨርሲቲው በተጨማሪም 3 መቶ ፍየሎችን አስረክቧል።
የቀብሪደሃር ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች አገልግሎት ሀላፊ አቶ ዳንኤል ግርማ ፣ የሽብር ቡደኑ እስከሚደመስሰ ደረስ ድጋፍ በማድረግ ደጀንነቱን እንቀጥላለን ብለዋል ።
የመከላከያ ፋይናንስ ስራ አመራር ዘርፍ ተወካይ ብ/ጀ አለምሰገድ ወንድወሰን በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያ ህዝብ አዲስ ምልምል ሰልጣኞች ወደ ማሰልጠኛ በመላክና ድጋፍ በማድረግ ሀገራዊ ግዴታውን እየተወጣ መሆኑን ገልፀው ፣ የቀብሪደሃር ዩኒቨርስቲ ላደረገው ድጋፍም ማመስገናቸውንከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!