አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋሊ ኮማ ቀበሌ በንጹሀን ዜጎች ላይ በሽብርተኛው የህወሓት ቡድን የተፈጸመውን ጭፍጨፋ የሚያወግዝ ሰልፍ በዲግ ዲጋ ተካሄደ።
በአፋር ክልል ፊንቲ ረሱ ዞን ዲግ ዲጋ ቀበሌ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በሽብርተኛው ቡድን ጥቃት የቤተሰብ አባሎቻቸውን ያጡ የጥቃቱ ሰለባዎች ተሳትፈዋል።
ሽብርተኛው የህወሓት ቡድን በጋሊኮማ ንጹሀን ዜጎች ላይ የፈጸመውን ጭፍጨፋ መቼም አንረሳውም፣ ጁንታው የአፋር ህዝብ ጠላት ነው፣ አፋርን መጎብኘት እንጂ መንካት ራስን ኤርታሌ ውስጥ እንደመክት ነው፣ የጋሊኮማውን ጭፍጨፋ የአለም ህዝብ ሊያወግዘው ይገባል የሚሉ መልእክቶች በሰልፉ ተስተጋብተዋል፡፡
አያቶቻችን ያስተማሩን ኢትዮጵያዊነትን ማክበር ነው ያሉት ሰልፈኞቹ÷ የአፋርን ህዝብ መረማመጃ አድርጎ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ማሰብ የማይቻል መሆኑንም ነው የገለፁት፡፡
በሽብርተኛው ቡድን ሀብት ንብረታቸውን ላጡ ዜጎችም ድጋፍ እንዲደረግ በሰልፉ ላይ ተጠይቋል።
በጥበበስላሴ ጀምበሩ እና ሀቢብ አደም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

