አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ አፋር ክልል ሰርጎ የገባውን የህወሓት አሸባሪ ቡድን ከገባበት ሳይወጣ ለመደምሰስ የጸጥታ ሃይሉ በቅንጅት እየሰራ መሆኑን የአፋር ክልል ልዩ ሃይል ምክትል አዛዥ ኮማንደር መሃመድ ሰናይ ገለጹ።
የአፋር ክልል ልዩ ሃይል ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር በመቀናጀት ወደ ክልሉ ሰርጎ የገባውን የህወሓት አሸባሪ ቡድን ለመደምሰስ በቅንጅት እየተሰራ ነው ብላዋል፡፡
በእስካሁኑ የህልውና ዘመቻ በርካታ የአሸባሪው ቡድን ታጣቂዎች ሲደመሰሱ የተማረኩም እንዳሉ ጠቅስዋል።
ቡድኑ ከባድ መሣሪያ ህዝቡ ላይ በመተኮስ በበርካታ ንፁሃን ላይ የፈፀመውን ድርጊት አስታውሰው÷ አሁን ላይ የተቀናጀ እርምጃ እየተወሰደበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የአፋር ክልል ልዩ ሃይል ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር በመቀናጀት የጥፋት ቡድኑን በመመከት ወደ ኋላ እንዲሸሽ አድርጓልም ነው ያሉት፡፡
በክልሉ አራት ወረዳዎች ሰርጎ የገባውን አሸባሪ ቡድን ለመደምሰስ የተቀናጀ ዘመቻ እየተከናወነ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
ጋሊኮማ በተባለ ቦታ ጥቃት ያደረሱ የአሸባሪ ቡድኑ ታጣቂዎች ብዙዎቹ መደምሰሳቸውን ምክትል አዛዡ ተናግረዋል፡፡
አሸባሪው ኪልባቲ ረሱ በራህሌ ወረዳ ሰሞኑን ጥቃት መፈጸሙን አስታውሰው÷ በአጸፋው የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድበት መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

