Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የፌዴራል ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች ለአገር መከላከያ ሠራዊት የ1 ወር ደሞዛቸውን እና ደም ለገሱ፡፡
ህወሓት በእብሪት ተነሳስቶ የኢትዮጵያን አንድነት ከማይፈልጉ ጠላቶች ጋር ሆኖ ኢትዮጵያን ለመበታተን እየሰራ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነር ወዶ አጦ ገልፀዋል።
በዚህም ተጋድሎ እያደረገ ካለው መከላከያ ጎን ሆኖ አጋርነትን ለማሳየት የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ከ አንድ ወር ደመወዛቸው 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በተጨማሪ ደም ልገሳ ማድረጋቸውን ነው የተናገሩት።
ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ተወካይ ሌተናንት ኮሎኔል አበራ ነጋሳ በሽብር ቡድኑ ላይ እየተወሰደ ባለው ዘመቻ ድሎች እየተመዘገቡ መሆኑን መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version