Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ ከቻይና መንግስት የተላከላትን የኮቪድ19 መከላከያ ክትባት ተረከበች

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከቻይና መንግስት የተላከላትን 300 ሺህ ዶዝ የኮቪድ19 መከላከያ ክትባት ተረከበች።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እና በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዥያዎ ዢዮዋን በተገኙበት ክትባቱ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ርክክብ ተደርጓል።
አምባሳደሩ ዢዮዋን ቻይና ኢትዮጵያ የኮቪድ19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት በምታደርገው ጥረት አጋር መሆኗን አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።
ቤጂንግ በኮቫክስ ጥምረት በኩል 300 ሺህ ዶዝ የኮቪድ19 መከላከያ ክትባት መላኳንም ገልፀዋል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ፥ክትባቱ ተጠናክሮ ለቀጠለው የመከላከል ጥረት እንደሚያግዝ ጠቅሰው፥ የቻይና መንግስት ላደረገው ድጋፍም ሚኒስትሯ አመስግነዋል።
ክትባቱ በዋናነት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚውልም ተነግሯል።
ቻይና በዛሬው ዕለት የላከችውን 300 ሺህ ዶዝ ክትባት ጨምሮ እስካሁን ባለው ሂደት ለኢትዮጵያ 1 ሚሊየን ዶዝ የኮቪድ19 መከላከያ ክትባት ድጋፍ ማድረጓን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share
Exit mobile version