Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የዩኒቨርሲቲው መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሰራዊቱ ሀገርን ለማዳን ህይወቱን ሲሰዋና ሲታገል እኛም በምንችለው ከጎኑ ልንሆን ይገባል በማለት የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ድጋፍ አደረጉ፡፡
ከዚህ ቀደምም ድጋፍ ሲያደርግ የቆየው ዩኒቨርሲቲው÷ አሁንም ከደመወዝ በተጨማሪ የደም ልገሳ መርሃ ግብር መካሄዱን የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር መልካሙ ማዳ ተናግረዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በቀጣይም በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ በመሳተፍ ለመከላከያ ሰራዊቱ አጋርነቱን አጠናክሮ ይቀጥላልም ነው የተባለው፡፡
በታሪክነሽ ሴታ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version