Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለመከላከያ ሰራዊት እና ለተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለመከላከያ ሰራዊት እና በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
የዩኒቨርሲቲው ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ሰለሞን እደገለፁት÷ ህወሓት ያለፈ በደሉን በይቅርታ ሲታለፍ ዳግም በንጹሀን ላይ ግፍ እየፈጸመ ነው ብለዋል፡፡
በዚህም ዩኒቨርሲቲው ህግን በማስከበር ተግባሩ ከመንግስት ጎን መሆኑን ነው ያስረዱት፡፡
ለመከላከያ ሰራዊት እና ለተፈናቃይ ወገኖች የሚሆን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ ምግብ፣ የቤት ቁሳቁስ፣ የንጽህና መጠበቂያ እና አልባሳት ይገኙበታል ተብሏል፡፡
በዚህ ለተፈናቃይ ወገኖች የተደረገውን ድጋፍ ወሎ ዩኒቨርሲቲ÷ ለመከላከያ ሰራዊት የተደረገውን ድጋፍ ደግሞ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተረክበዋል ተብሏል፡፡
በአለባቸው አባተ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version