አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢሲ) በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰባቸው ያለውን እስር፣ ግፍ እና መከራ የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ አዲስ አበባ በሚገኘው የሳውዲ ኢምባሲ ተካሂዷል።
እኔም ለወገኔ ድምፅ ነኝ በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ÷ በሳዑዲ በእስር በሚገኙ ሴቶች ህጻናት እና ወጣቶች ላይ እየተፈጸመባቸው ያለው ግፍ እንዲቆም ጠይቀዋል።
ሳዑዲ በኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸመች ያለችው ኢሰብዓዊ ድርጊት በማቆም በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው እንድትመልስ ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል።
በሳውዲ በእስር ላይ 80 ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

