Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ህወሓትን ለመደምሰስ አርሶ አደሩና ወጣቶች በግንባር ደጀንነታቸውን እያሳዩ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለመደምሰስ አርሶ አደሩና ወጣቶች በግንባር ደጀንነታቸውን እያረጋገጡ ይገኛሉ።
 
በወሎ ግንባር የሽብር ቡድኑን ለመደምሰስ መከላከያ ሰራዊት፣ የክልሎች ልዩ ሃይሎችና ሌሎች የጸጥታ ሃይሎች የተቀናጀ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ናቸው፡፡
 
አርሶ አደሮችና የአካባቢው ህብረተሰብ መረጃ በማቀበል፣ ቁስለኞችን በመንከባከብና ህክምና እንዲያገኙ በማድረግ እንዲሁም ለወገን ጦር ስንቅ በማቃበል የህዝብ የሆነውን ሰራዊት በማበረታታት ላይ ይገኛሉ፡፡
 
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ውጊያ በተካሄደባቸው የተለያዩ ግንባሮች በመገኘት በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለመከላከያ ሰራዊት የሚደረገው ድጋፍ መቀጠሉን አረጋግጧል።
 
ሃሳባቸውን የሰጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ዳግም ባርነትን ላለመቀበልና አሸባሪውን ቡድን ለመደምሰስ ከድጋፍ ባሻገር መስዕዋትነትን ለመክፈል ተዘጋጅተናል ነው ያሉት።
 
በግንባር ጠላትን እየደመሰሱ የሚገኙ የሰራዊቱ አባላት በበኩላቸው÷ ከህዝቡ እየተደረገልን ያለው ድጋፍ ለበለጠ ድልና አሸናፊት የሚያዘጋጀን ነው ብለዋል፡፡
 
በአፈወርቅ እያዩና ለይኩን ዓለም
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version