Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኪነ ጥበብና ባለሙያዎቹ መኖር የሚችሉት ሀገር ሲኖር ነው-የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አመራርና ሰራተኞች ከኦሮሞ ባህል ማዕከልና ከኦሮሞ አርቲስቶች ማህበር ጋር በመሆን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ዛሬ የደም ልገሳ መረሃ ግብር አካሄዱ፡፡
በደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ከበደ ዴሲሳ እንዳሉት÷ ኪነ ጥበብና ባለሙያዎቹም መኖር የሚችሉት ሀገር ሲኖር ነው፡፡
በሀገሪቱ እየታየ ላለው ለውጥ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ሚና የጎላ መሆኑን የጠቀሱት ሃላፊው÷ በቀጣይም አሸባሪው ህወሓትና ተላላኪዎቹን ለማጥፋት ግንባር ላይ ህይወቱን እየሰጠ ካለው መከላከያ ሰራዊት ያልተናነሰ ስራ ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት።
የተጋረጠብንን አደጋ ለመቀልበስና ለልጆቻችን የተሻለ ሀገር ለማስቀጠል ሁሉም ሰው ባለው አቅምና ችሎታ መረባረብ አለበት ብለዋል።
የኦሮሞ አርቲስቶች ማህበር ሊቀመንበር አርቲስት ሞአታ ሸኒ በበኩሉ÷ አሁን ጊዜው ሆኖ ሀገር በማዳን ጥሪ ውስጥ ደማችንን ለመከላከያ ሰራዊቱ በመለገሳችን እድለኞች ነን ሲል ገልጿል።
ግንባር ድረስ ሄደን ለመከላከያ ሰራዊታችን አጋርነታችንን ለማሳየት ዳግም ቃል የምንገባበት መርሃ ግብር ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version