አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ወሎ ግንባር ከተሰለፈው መከላከያ ሰራዊት ጋር በቅንጅት በመስራት ህውሓትን እስከ መጨረሻው ለመደምሰስ ጠንክረው እንደሚሰሩ የውርጌሳ ከተማ ወጣቶች ገለጹ።
በቀጠናው የሚገኙ የሠራዊት ክፍሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የከተማው ነዋሪዎች በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
በውይይት መድረኩ የሰራዊቱ አመራሮች ወጣቱ ለጸጥታ ሃይሎች የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አድንቀዋል ።
የሠራዊት ክፍሉ ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክተር ተወካይ ሌተናል ኮሎኔል ለችሳ መገርሳ ÷ የውርጌሳ ከተማ ህዝብ ለማንነቱ የታመነ በህልውናው የማይደራደር ኩሩ ህዝብ መሆኑን አውስተዋል፡፡
ይህንም ከሰራዊቱ ጎን ተሰልፎ በሰራው አኩሪ የጀግንነት ተግባር አረጋግጧል ነው ያሉት፡፡
የሠራዊት ክፍሉ የሰው ሃይልና የመሳሪያ ዝግጅት ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል አየነው አበበ በበኩላቸው÷ ሃገርን አፈርሳለሁ ብሎ የተነሳው የጥፋት ሃይል ድል የሚደረገው ጠንካራ የሗላ ደጀን ባለው ህዝባዊ ሰራዊት መሆኑን በውል በመረዳት ነዋሪዎች ያደረጉት ንቁ ተሳትፎ የሚደነቅ መሆኑን ጠቁመዋል ።
የከተማው ወጣቶችም ተተኳሽ በማቅረብ ፣ ስንቅ በማቀበልና ፊትለፊት ተሰልፎ በመዋጋት የጁንታው ቡድን ግብዓተ መሬቱ እስከሚፈጸም ተደራጅተን በቁርጠኝነት እንሰራለን ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

