Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ለህልውና ዘመቻው 265 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ለህልውና ዘመቻው 265 ሚሊየን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ኃይለ ማርያም፥ የህውሓት የሽብር ቡድን በሀገራችን ብሎም በክልላችን ላይ የሠነዘረውን የወረራ ሙከራ ለመመከት የዞኑ ህዝብና መንግስት በትብብር እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡
በዞኑ እስካሁን ድረስ ከ367 ቀበሌዎች የተወጣጡ ሰልጣኞች ለህልውና ዘመቻው እየሰለጠኑ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡
ለህልውና ዘመቻው ከ300 ሚሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ እስካሁን ድረስ 265 ሚሊየን ብር መሰብሰቡን ነው አቶ ወርቁ ኃይለ ማርያም የተናገሩት፡፡
በማህበረሰብ ስንቅ ደግሞ ደረቅ ሬሽን እና የቀንድ ከብት መሰብሰቡ የተገለፀ ሲሆን÷ ይህም በገንዘብ ሲተመን ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ነው ተብሏል፡፡
ከተሰበሰበው ውስጥም እስካሁን ድረስ 24 የቀንድ ከብት እና ከ10በላይ ፍየሎች ለማይ ጋባ ግንባር እንዲሁም 27 የቀንድ ከብት ለሠሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር ማስረከባቸውን ገልፀዋል።
የዞኑ የመንግስት ሰራተኞችም በዓመት የሚከፈል ሙሉ የወር ደሞዛቸውን የለገሡ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ በአካል ዘመቻውን ለመቀላቀል ከ300 በላይ የሚሆኑ ሠራተኞች ሰልጥነው እየተጠባበቁ ነው ብለዋል፡፡
በኤልያስ አንሙት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
549
Engagements
Boost Post
522
4 Comments
23 Shares
Like
Comment
Share
Exit mobile version