Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የህወሓትና ሸኔ የሽብር ቡድኖችን እንቅስቃሴ ለመግታት በቂ ዝግጅት ተደርጓል- የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል፣ የክልልና የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በባቲ ግንባር የተሰማራውን ሚሊሻ ጎብኝተዋል።
የልዩ ዞኑ ወረዳዎች፣ ከደቡብ ወሎና የአፋር ክልል የሚዋሰኑባቸው ቦታዎች ላይ የተሰማራው ሚሊሻ የሽብር ቡድኖቹ ሰርገው መግባት የሚችሉበትን መንገድ ሙሉ ለሙሉ ዘግተናል ብሏል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አህመዲን መሐመድ፥ አመራሩ፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የፀጥታ ኃይሉ የሽብር ቡድኖቹን ለመመከት ያደረጉትን ዝግጅት አድንቀዋል።
መተባበር ከቻልን አንዳች ኃይል አይደፍረንም ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው÷ የስጋት ቦታዎችን ሁሉ በመድፈን ህዝባችንን ከስጋት ነፃ ማድረግ አለብን ብለዋል።
የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ሐሰን ፥ የህዝባችን ጠላት የሆኑትን የህወሃትና የሸኔ ቡድኖችን የሰርጎ ገብ እንቅስቃሴ ለመግታት ሚሊሻው በአስተማማኝ ቁመና ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊ ፍቅረማርያም ደጀኔ በበኩላቸው ፥የኢትዮጵያውያን ሁሉ ጠላት የሆኑትን ቡድኖች ለመመከት ትብብር ወሳኝ ነው ማለታቸውን ከሰሜን ሸዋ ዞን ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version