አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 118፣ 2013 (ኤፍቢ ሲ)በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጀሞ አካባቢ 6ኛው የተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከል ቅርንጫፍ ተከፍቶ ስራ ጀምሯል።
ማዕከሉ በቀን 2 ሺህ ሰዎችን መመገብ የሚችል አቅም አለው።
በጎፈቃደኛ የሆኑት አቶ ሽኩር ለአንድ ዓመት የሚቆየውን የማዕከሉን የምገባ ወጪም እንደሚሸፍኑ ተገልጿል።
ማዕከሉን መርቀው ስራ ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፥የምገባ ማዕከሎቹን የምንከፍተው ከቆሻሻ ላይ ጭምር ምግብ እየፈለጉ የሚበሉትን ወገኖቻችን ካለን እያካፈልን እነሱም ንጹህ ምግብ እንዲበሉ ለማድረግ ነው ብለዋል።
የሀገራችንን እና የዜጎቻችንን ክብር ማስጠበቅ የምንችለው እንደዚህ ሁላችንም የሚጠበቅብንን ስንሰራ ነውም ብለዋል።
በዘመን በየነ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

2,580
People Reached
166
Engagements
Boost Post
135
3 Comments
5 Shares
Like
Comment
Share

