አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ትዝታ ሙሉጌታ ከፓራዳይዝ ግሩፕ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ማዩር ዶሺ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው አምባሳደር ዶክተር ትዝታ በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት እድሎች እንዲሁም ማበረታቻዎች አንስተዋል።
ድርጅቱ በኢትዮጵያ የሚያቀርበው የኢንቨስትመንት ፕሮፖዛል ተግባራዊነት አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።
ማዩር ዶሺ በበኩላቸው ፥ድርጅታቸው በሴራሚክ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የካበተ ልምድ ያለው መሆኑን ገልጸው ፥ በዘርፉ በኢትየጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት ያላቸው መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

