Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጀግኖች እና የህጻናት አምባ ለመከላከያ ሰራዊት የዓይነት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀግኖች እና የህጻናት አምባ ለመከላከያ ሰራዊት ጤና ዋና መምሪያ 12 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚያወጡ ቁሳቁሶችን ለገሰ።
የተደረገው ድጋፍም÷ ከ2ሺህ በላይ የታካሚዎች አልባሳት፣ 100 የህክምና አልጋ፣ 100 ፍራሽ እና 8 ቴሌቪዥኖች ናቸው።
ግንባር ላይ ለሚዋደቀው ሠራዊት አጋርነታቸውን ለመግለጽ በካናዳ የሚኖሩት አቶ መላኩ ሰዩም እና ዶክተር ጌታቸው ለዚህ ድጋፍ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን የብሄራዊ ጀግኖች እና ህጻናት አምባ ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር አዳሙ አንለይ ተናግረዋል፡፡
የጀግኖች እና ህጻናት አምባ አማካሪ ብርጋዲየር ጀኔራል ካሳዬ ጨመዳ በበኩላቸው÷ የሠራዊቱ ጉዳት ጉዳታችን በመሆኑ በሽብርተኛው ቡድን የተጎዱ አባላትን ለማከም የሚረዱ ቁሳቁሶችን አሰባስበናል ብለዋል፡፡
የጦር ሀይሎች ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አዛዥ እና የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ተወካይ ብርጋዲየር ጀኔራል ዶክተር ሀይሉ የብሄራዊ ጀግኖች እና ህጻናት አምባ ከዚህ በፊትም ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰው አሁንም ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version