Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የኦሮሚያ እና የአማራ ክልል የንግድ ቢሮዎች ገለጹ።
የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ ወርቁ ጫላ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ ህገ ወጥ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
እስካሁንም ባለው ሁኔታም ችግር ሊኖርባቸው ይችላል ተብለው ከተለዩት ከ33 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ውስጥ ከ11ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቀዋል፡፡
ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የቢሮ ሃላፊው አቶ ወርቁ ጫላ ገልጸውልናል፡፡
በአማራ ክልል ምርት መደበቅ እና አላስፈላጊ ዋጋ መጨመር በስፋት እየተስተዋለ መሆኑን የገለጹት የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ አበባው ውቤ ናቸው፡፡
የአንዳንድ ነጋዴዎች ተግባር ለሀገር እና ለዜጎች ካለማሰብም ባለፈ ሀገርን ለማፍረስ ከተነሳው አሸባሪ የህወሓትቡድን ተለይቶ እንደማይታይ ገልጸዋል፡፡
በተደረገው ቁጥጥር እና ክትትል ከ7 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ የቅጣት እና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ጠቅስው÷ ህጉን ተከትለው በማይሰሩ ህገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ የሚወሰደው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
በሲሳይ ጌትነት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version