Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ 5 ሺህ 726 ተማሪዎችን ያስመርቃል

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በነገው ዕለት ለ13ኛ ጊዜ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 5 ሺህ 726 ተማሪዎች ያስመርቃል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በዋናው ግቢ ፣ በኦቶና ማስተማሪያና ሪፌራል ሆስፒታል እንዲሁም በታርጫ ግቢ በመደበኛ፣ በሳምንት መጨረሻ ቀናትና በምሽት መርሐ ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 3 ሺህ 304 ወንድና 1 ሺህ 964 ሴት ተማሪዎችን ነው የሚያስመርቀው፡፡

እንዲሁም በሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት መርሐ ግብር 385 ወንድና 63 ሴቶችን ሲያስመርቅ በሶስተኛ ዲግሪ ስድስት ወንድና አንድ ሴት እጩ ዶክተሮችን ያስመርቃል።

ከእነኝህ ውስጥ በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ 185 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲውያስቀራል ነው የተባለው።

በምረቃው መርሐ ግብሩ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በአበበች ኬሻሞ እና በመለሰ ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version