አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን ብሔራዊ የጸጥታ ሚኒስትር ኦቡት ማሙር ሜቴ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ።
በውይይቱ አምባሳደር ነቢል የአገራቱ የቆየ ግንኙነት ዘመን ተሻጋሪ መሆኑን በማውሳት ግንኙነቱን የበለጠ ለማጠናከር በሁለቱም ወገን ጠንካራ ቁርጠኝት መኖሩን ገልጸዋል።
በተጨማሪ አምባሳደሩ በሕዳሴ ግድብ ድርድር ሂደት፣ የትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ለሚኒስትሩ ገለጻ አድርገዋል።
ኦቡት ማሙር በበኩላቸው÷ ደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ግንኙነት በጥልቅ መሠረት ላይ የተገነባ መሆኑን ገልጸዋል።
የደቡብ ሱዳን ነጻነት የኢትዮጵያ ድጋፍ ባይታከልበት እውን መሆኑ አጠራጣሪ ነበር ያሉት ሚኒስትሩ ግንኙነቱ በወቅታዊ ሁኔታዎች የማይለዋወጥ መሆኑን ተናግረዋል።
በተያያዘ የኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ለደቡብ ሱዳንም ሆነ ለአካባቢው ትልቅ ጥቅም ያለው መሆኑን በመግለጽ የምስራቅ አፍሪካ አገራት ትብብርን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን መጠቆማቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

