Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አሸባሪው ህወሓት የትግራይ ወጣቶችን አስገድዶ እያስፈጀ መሆኑን በማይጸብሪ ግንባር እጃቸውን የሰጡ የቡድኑ አባላት ተናገሩ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት የትግራይ ወጣቶችን አስገድዶ በጦርነት በመማገድ እያስፈጀ መሆኑን በማይጸብሪ ግንባር ለተሰማራው የፀጥታ ሀይል እጃቸውን የሰጡ የአሸባሪ ቡድኑ አባላት ተናገሩ፡፡

አሸባሪ ቡድኑ ከእያንዳንዱ ቤተሰብ ቢያንስ ሁለት የቤተሰብ አባላት ወደ ጦርነት በግዴታ እንዲገቡ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ምንም አይነት ወታደራዊ ስልጠና ሳይወስዱ የተለያዩ ተተኳሾችን ለመሸከምና ቁስለኞችን ለማግለል በሚል ወደ ጦርነት እንዲገቡ መደረጋቸውንም ተናግረዋል፡፡

የትግራይ ህዝብ አሁን ላይ ልጆቻችን የት አሉ? የጦርነቱ አላማስ ምንድን ነው በሚል አሸባሪው ህወሓትን እየጠየቀ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

እያንዳንዱ ቤተሰብ ካለው የቤተሰብ አባል ሁለትና ሶስት ጨምሮ በማስመዝገብና እርዳታ በመቀበል ለአሸባሪ ቡድኑ እንዲሰጥ እየተደረገ መሆኑንም መጠቆማቻን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

እጃቸውን ከሰጡ በኋላ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version