Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአዲስ አበባ ለዘማች ቤተሰቦች ድጋፍ እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር የመከላከያ ሠራዊቱን ለተቀላቀሉ የዘማች ቤተሰቦች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡

የማህበሩ ስራ አስፈፃሚ ወጣት ታምራት ሚሊዮን ማህበሩ የዘማች ቤተሰቦችን ቤት በማደስና የሴፍቲኔት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ ማመቻቸት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ነው የገለጸው፡፡

ማህበሩ መጪውን አዲስ ዓመት በማስመልከት ዕለቱን ከዘማች ቤተሰብ ጋር እንደሚያሳልፍ ተገልጿል፡፡

እስካሁን በመዲናዋ የ46 የዘማች ቤተሰቦችን ቤት አድሰናል ብለዋል ሥራ አስፋጻሚው፡፡

ኢትዮጵያውያን “ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ፤ የትም፣ መቼም፣ በምንም!” በሚል መሪ ሃሳብ የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተቀብለው የሚጠበቅባቸውን ሚና እየተወጡ ይገኛሉ ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

Exit mobile version